Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Jan 2025, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Forest And Tree Sales

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በራጴ ወረዳ በራጴ ቶራ ቀበሌ ከዞን 25 ኪ/ሜ በራጴ ወረዳ መቀመጫ ላይ የሚገኘውን 9.2 ሔክታር የሚሆን የባህርዛፍ ደን በአዋጁ መሰረት የዞንና የወረዳ ባለሙያ ባደረገው ጥናት መሠረት የራጴ ወረዳ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


ግልጽ  ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በራጴ ወረዳ በራጴ ቶራ ቀበሌ ከዞን 25 ኪ/ሜ በራጴ ወረዳ መቀመጫ ላይ የሚገኘውን 9.2 ሔክታር የሚሆን የባህርዛፍ ደን በአዋጁ መሰረት የዞንና የወረዳ ባለሙያ ባደረገው ጥናት መሠረት የራጴ ወረዳ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት
  2. ፍቃዱን በበጀት ዓመቱ ያሳደሰ/ች
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ያላት
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል፤
  5. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች /ድርጅት/ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር ላይ መሉ ክፍያ በመፈፀም ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራች /ድርጅት/ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ክፍያ በተባለው ጊዜ ባይፈጽም ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የሚወሰድበት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ባህር ዛፉን /ደኑን/ የጎበኙበትን ማስረጃ ከራጴ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ደን ልማት ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ የምትወስዱ ይሆናል።
  9. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ5፡30 ታሽጎ 6፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ኦሪጅናል አንድ፣ ኮፒ ሁለት በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ሕጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  11. የጨረታ ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ከሌለበት ዋጋ አይኖረውም ፡፡

ማሳሰቢያ ፡- የተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት ማስተጓጎል አይችልም። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የሚከፈትነት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ለበለጠ  መረጃ ፡- 09-33-11-31-36 / 0932 46 01 71

 

በደቡብ  ኢትዮጵያ  ክልል  በጌዴኦ  ዞን  በራጴ  ወረዳ  ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender