Tender Detail

Tender Details

  • Company የ
  • Address , Phone: 057-660-37-97
  • Website
  • Deadline31 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ አይነት ጎማ እና ካነመዳሪያ (Tyer with Inner tube) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የ


የጨረታ  ማስታወቂያ  የጨረታ  ቁጥር

OSE/007/2017

 

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2017 በጀት ዓመት:

የተለያዩ አይነት ጎማ እና ካነመዳሪያ (Tyer with Inner tube) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

  1. ተጫራቶች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ በማስላት ይግባ) የብር መጠኑ ስሌት ከብር 500,000.00 ከበለጠ ተጫራቾች ማስያዝ ያለባቸው ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ፣ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ባንከ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተያያዘው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን (ሶፍት ኮፒ) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ ዋና መስሪያ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 402 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የቴክኒክ እና የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ 7፡30-11:30 ነው::

ለበለጠ ማብራሪያ፡-

ስ.ቁ 011-416 03/09/011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡

 

የኦሮሚያ  ምርጥ  ዘር  ኢንተርፕራይዝ

Save Tender