የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በዋስትና ንግድ ማዕከል ህንጻ ለንግድ አገልግሎት የሚሆን የኪራይ ቦታ ለማከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በዋስትና ንግድ ማዕከል ህንጻ ለንግድ አገልግሎት የሚሆን የኪራይ ቦታ ለማከራየት ይፈልጋል።
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ግዥ ክፍል በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ጨረታው የሚከፈተው የጨረታው ማስታወቂያ በመጣበት በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
አድራሻ ፡- ከ4 ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ፊት ለፊት ሲሆን
በስልክ ቁጥር ፡- 0111232705 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ ፡- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኪራይ ቦታ ዋጋ በግልፅ መሞላት ይጠበቅባቸዋል። አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
