Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ሪጅን ማይጨው ቅርንጫፍ
  • Address ማይጨው ቅርንጫፍ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0347770289
  • Website
  • Deadline31 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኣስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ሪጅን ማይጨው ቅርንጫፍ


 

ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኣስተዳደር ማይጨው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-

  1. ቤቱ ሙሉ ግቢ ህንጻ ሆኖ 14 ክፍሎች ያሉትና (እያንዳንዱ ከፍል ስፋት ቢያንስ 3x4 የሆነ) ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት አመቺና ለዋና መንገድ ቅርብ የሆነ፣
  2. የጽ/ቤቱን ሰራተኞች እና ተገልጋዮች ከሚያውኩ የድምጽ ብከለት የራቀ እንዲሁም አጎራባች ቤቶች እና ሕንጻ ውስጥ የቢሮ አገልግሎቱን የሚያውኩ ሁኔታዎች የሌለው፣
  3. የይዞታ ካርታ እና ዓመታዊ ግብር የተከፈለ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ፣
  4. የራሱ የሆነ መጸዳጃ ቤትና የጥበቃ ቤት ያለው፣
  5. የራሱ የሆነ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ የውሃና የስልክ መስመር ያለው፣
  6. ለሚያከራየው ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆነ በሚቀርበው ዋጋ ላይ ቫት ስለመካተቱ መግለጽ የሚኖርበት ሲሆን ኪራይ ቆይታ ጊዜ ለ3 ዓመት ውል መግባት ፈቃደኛ የሆነ፣
  7. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ከሰሜን ሪጅን የማይጨው ቅ/ጽ/ቤት ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  8. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሰሜን ሪጅን ማይጨው ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ መመለስ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የዕረፍት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ዕለት በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን። በዚሁ መሰረት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ክፍሎችን ብዛት እና ስፋት በግልጽ በካሬ ሜትር፣ የአንድ ወርና የአንድ ዓመት ክፍያን በማስላት በተዘጋጀው ሠንጠረዥ ውስጥ መግለጽ አለባቸው።

ለበለጠ  መረጃ  ስልክ ፡- 0347770289

የመንግስት  ሰራተኞች  ማህበራዊ  ዋስትና  አስተዳደር

ሰሜን  ሪጅን

ማይጨው  ቅርንጫፍ

Save Tender