Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Governmnet Bureau of Justice (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ)
  • Address ሜክሲኮ ፊሊፕስ አጠገብ ወይም ጨለለቅ አልሳም ታወር ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115159548
  • Website
  • Deadline25 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በድጋሚ ለቢሮው አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa City Governmnet Bureau of Justice (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ)


ግልጽ  የግዥ  ጨረታ  ማስታወቂያ

ፍ/ቢ  ቁጥር  002/2017 /በድጋሚ/

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በድጋሚ ለቢሮው አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

 

ሎት አንድ

የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ላፕቶፕ ፣ ኮምፒውተር፣ ኤልሲድ ማስታወቂያዎች፣ ቴሌቪዥኖች ዋየርለስ ማይኮች ወዘተ

ሎት ሁለት

በቢሮ ለሚደረጉ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚውል የታሸገ ውሀ /አምራች ድርጅቶች ቢሆኑ ይመረጣል/፣ ቆሎ፣ ድፎዳቦ /የአበሻ ውል ገብቶ ማቅረብ የሚችል

ሎት ሶስት

የተለያዩ ህትመቶች/ የህትመት ውጤቶች፣ ባነሮች፣ የአቅጣጫ መጠቆሚያዎች ወዘተ

ሎት አራት

የተለየዩ መጋረጃዎች፣ የወለል ምንጣፎች ግዥ፣ የአበባ ማስቀመጫ ፖቶች/የቢሮው አርማ ያለበት/

ሎት አምስት

ለተለያዩ ስልጠናዎችና ስብሰባዎች የሆቴል አገልግሎት

ሎት ስድስት

የተለያዩ የመኪና እቃዎች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማዎች ቸርኬዎች የጎማ ከቨሮች፣ ባትሪዎች ወዘተ

ሎት ሰባት

አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የፅዳት እቃዎች ግዥ የፕሪንተር ቀለሞች ፎቶ ኮፒ ቀለሞች ..ወዘተ

ሎት ስምንት

የኤሌክተሪ የቧንቧ እቃዎች

ሎት ዘጠኝ

የስራ ልብስ ግዥ እና የስፌት ግዥ ጫማዎች የሴትና የወንድ ቦርሳዎች

ሎት አስር

ወንበሮች ጠረጴዛዎች የአስተያት መስጫ ሳጥኖች

 

  1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውንና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ፣
  4. በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ታግዶ የነበረ ከሆነ የዕገዳ ጊዜውን ያጠናቀቀ፣
  5. ውል ለመፈፀም የሚያስችል የሕግ ችሎታ ያለው፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በግዥ ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ኛ ፎቅ ላይ በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ስም ለሎት አንድ ብር 3,000፣ ለሎት ሁለት ብር 2,000፣ ለሎት ሦስት ብር 2,000፣ ለሎት አራት ብር 5,000፣ ለሎት አምስት ብር 6000፣ ለሎት ስድስት ብር 5,500 ፣ ለሎት ሰባት ብር 4,000፣ ለሎት ስምንት ብር 2000፣ ለሎት ዘጠኝ ብር 3,000፣ ሎት አስር 6000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡ 
  8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላትና ማህተም በማድረግ ፖስታቸውን በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የቴክኒካል ሠነድ ኦሪጅናልና ኮፒ፣ የፋይናንሻል ሠነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተገዛው ሰነድ ላይ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው አቅርቦት መጠን በላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 25% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰአት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ጠዋት 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር ፡- 0115159548 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻችን ፡- ሜክሲኮ ፊሊፕስ አጠገብ ወይም ጨለለቅ አልሳም ታወር ፊት ለፊት

 

የአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር  ፍትሕ  ቢሮ

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE