ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሎት 1- የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ጃኬት፣ ሱሪ እና ፖሎ ቲ-ሸርት) ሎት 2- የጽዳት ሰራተኞች ፕላስቲክ ነጠላ ጫማ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ CN/NCB/12/17
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ
ሎት 1- የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ጃኬት፣ ሱሪ እና ፖሎ ቲ-ሸርት)
ሎት 2- የጽዳት ሰራተኞች ፕላስቲክ ነጠላ ጫማ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100 በመከፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ዶከመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረት ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለ ተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ስልከ ቁጥር 0111569992 አዲስ አበባ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
