የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመሀል ሪጅን አምቦ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር መሀል ሪጅን አምቦ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለመሀል ሪጅን አምቦ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ፤
- ቤቱ ሙሉ ግቢ ወይም ህንጻ ሆኖ አጠቃላይ ስፋት ከ300 ካሬ ያላነሰ ጊቢ እና ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት አመቺ የሆነና ለዋና መንገድ ቅርብ የሆነ፡፡
- የጽ/ቤቱን ሠራተኞች እና ተገልጋዮች ከሚያውኩ የድምፅ ብክለት የራቀ እንዲሁም አጎራባች ቤቶች እና ህንፃ ውስጥ የቢሮ አገልግሎትን ከሚያውኩ ሁኔታዎች የሌለው::
- የይዞታ ማረጋጐጫ ካርታ እና አመታዊ ግብር የተከፈለ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ፣
- የራሱ የሆነ መፀዳጃ ቤትና የጥበቃ ቤት ያለው፡፡
- የራሱ የሆነ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ፣ የውሃ እና የስልክ መስመር ያለው፡፡
- ለሚያከራየው ቤት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ዋጋ ማቅረብ የሚችል እና ለ3 ዓመት ውል መግባት ፈቃደኛ የሆነ።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ከአምቦ ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአምቦ ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ መመለስ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚሁ መሰረት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ክፍሎቹን ብዛት እና ስፋት በግልጽ በካሬ ሜትር በማስፈር የአንድ ካሬ ሜትር ኪራይ ዋጋ ከተ.ዕ.ታ ጋር በማስላት አጠቃላይ ዋጋውን በካሬ ብዛት በተዘጋጀው ሰንጠረዥ ውስጥ መገለጽ አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- 011 2 60 97 97
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር መሀል ሪጅን አምቦ ቅ/ጽ/ቤት
