Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ ጠረንጴዛ፣ የካርድ ክፍል መደርደሪያ ሼልፍ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የህክምና መሳሪያዎች እና ካዝና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ ጠረንጴዛ፣ የካርድ ክፍል መደርደሪያ ሼልፍ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የህክምና መሳሪያዎች እና ካዝና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች፤
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ነች፤
  4. ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆነ/ነች 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  5. ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው።

ሎት 1 - ቋሚ እቃዎች፣

ሎት 2 - ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣

ሎት 3 - የህክምና መሳሪያዎች ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

  1. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሆስፒታሉ ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል።
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር የግዥ ኦፊሰር 09-14-34-43-06/ ፋይናንስ 09-34-37- 02-54/ የዋና ስራ አስኪያጅ 09-49-91-09-98 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

መካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

Save Tender