የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2017 በጀት ዓመት የሥራ ላይ አደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር :-RE-LP/OT/18/SIG/2017
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2017 በጀት ዓመት የሥራ ላይ አደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቶች ህጋዊ ለ2016/17 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No,) ሠርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/ አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በብር በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ሰዓት ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር ፡- +251-1-15-51-62-71 ወይም 115-50-04-17:
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25.000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ክቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
