Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Polytechnic College (የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
  • Address ደብረብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116815616
  • Website
  • Deadline17 Dec 2024, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለት/ክፍሎች እና ለስራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Polytechnic College (የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለት/ክፍሎች እና ለስራ ሂደቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን

      • የጽህፈት  መሳሪያ ፡- 6000
      • ኤሌክትሪክ  እቃዎች ፡- 10,000
      • ኮምፒውተር  እና  ተዛማጅ  እቃዎች ፡- 5,000
      • ህንፃ መሳሪያ ፡- 10,000
      • ጨርቃ  ጨርቅ ፡- 4,000
      • የጽዳት  እቃዎች ፡- 3,000
      • የአውቶሞቲቭ  የመለዋወጫ  እቃዎች ፡- 4,000

በአቅርቦቱ  መሳተፍ  የሚችሉ  ተጫራቾች

  1. ተጫራች የዘመኑን ፍቃድ ያደሱ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተቱትን ፎርማቶች ሞልተው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በትክክል በመሙላት በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም ሙሉ ስም እና ፊርማ በማድረግ ኦርጅናል ኮፒ ተብሎ ለየብቻው ተፅፎበት በፖስታ በማሸግ ጨረታው በዚህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ሰነዱን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የካላንደር በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ታሽጎ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም በውስጥ ማስታወቂያ ጭምር ይገለፃል።
  5. አንዱ ባቀረባው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  6. አሸናፊው ውል ገብቶ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  7. ግዥው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የግዥው መጠን 20,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ኮሌጁ የቫቱን ግማሽ ፐርሰንት ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑ ይታወቅ፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ማንኛውን ጥሬ እቃ ኮሌጁ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ለጨረታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በውስጥ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ከላይ በየሎቱ ፊት ለፊት በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የተዘጋጀ ጋጀውን ሰነድ እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ መቶ ብር/ ብቻ ለኮሌጁ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን መግዛት ለተከታታይ 15 ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ስልክ 0116815616/0116812572/12

 

የደ/ብርሃን  ፖሊ  ቴክኒክ  ኮሌጅ

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE