Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-122-00-20
  • Websitehttps://www.oromiaforest.et/
  • Deadline15 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች ለ2017 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተው የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፤ ብትን ጨርቆችን፤ ጫማዎችንና ሌሎች ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)


የሠራተኞች  ደንብ  ልብስ  ግዥ  ጨረታ  ማስታወቂያ

ጨረታ  ቁጥር ፤  ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ – 08/207

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች ለ2017 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተው የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፤ ብትን ጨርቆችን፤ ጫማዎችንና ሌሎች ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ እንዲትሳተፉ ድርጅቱ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል፤ አዲስ አበባ ከተማ ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ፤ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመታገዝ የደንብ ልብሱን ዝርዝር በማየት እያንዳንዱን ዕቃ/ልብስ የሚያቀርብበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንከ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንከ ዋስትና (Bank Guarantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከህዳር 24 ቀን 2017 ዓም እስከ ታህሣስ 6 ቀን 2017 ዓም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት ታህሣስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ከታች በገለጸው አድራሻ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣፣
  9. ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገለጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በጽሑፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ አራዳ ከ/ከተማ፤ ወረዳ 07፤ ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011-122-00-20/84 011-124-02-58

 

የኦሮሚያ  ደንና  ዱር  እንስሳት  ድርጅት

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE