Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

ድርጅታችን በ2017 በጀት ዓመት ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ግዥ ለማከናወን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ስለሚፈለግ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

   የጨረታ  ቁጥር  ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/ቅ/009/17

ድርጅታችን በ2017 በጀት ዓመት ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ግዥ ለማከናወን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ስለሚፈለግ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም  ተወዳዳሪዎች  የሚከተሉትን  መስፈርቶች  በማሟላት  በጨረታ  መሳተፍ  ይችላሉ::

  1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በገቢዎች ሚኒስቴር መ/ቤት በጨረታ እንዲሳተፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. በገንዘብ ሚኒስቴር (በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን መ/ቤት) ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬከቶሬት መግዛት ይቻላል፤
  6. ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝር መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 20 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስገባት የሚቻል ሆኖ በመጨረሻው 20ኛው ቀናት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 8፡30 ይከፈታል፣ የጨረታ ሠነዱን በአቅርቦትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬከቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ ህጋዊ የባንከ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፤ በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ቴክኒካል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ኮፒ በተለያየ የታሸገ ፖስታውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ኦርጅናል ሠነድም በተመሳሳይ ሁኔታ በማዘጋጀት የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  9. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  10. ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  11. የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 03 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ/የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ያሸነፈበትን ጥቅል ዋጋ ብር 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማል፤
  13. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀር ብዛት በ20% ለመጨመር/ለመቀነስ መብት አለው።
  14. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 20 ቀን ሆኖ በ20ኛው የመጨረሻው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  15. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- በስልክ ቁጥር 011 439 00 75/ 011 439 10 27 መጠየቅ ይችላሉ

አድራሻ ፡- አቃቂ  ቃሊቲ  ክፍለ  ከተማ  ከሸገር  ዳቦ  ፋብሪካ  ፊት  ለፊት  ትሬን  ባትሪ  መስጫ  ህንጻ  በስተጀርባ  70 ሜትር  ገባ  ብሎ  ነው፤

 

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት

Save Tender