ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ዋስትና የያዛቸውን ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሰረት ብድሩን ጊዜውን ጠብቀው ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2017
ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ዋስትና የያዛቸውን ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሰረት ብድሩን ጊዜውን ጠብቀው ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ሙሉ ስም |
የቀድሞው ቤቱ/ የንብረቱ ባለቤት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የንብረቱ ዓይነት |
የቦታው ስፋት |
የባለቤት መታወቂያ ቁጥር/ የሼር ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
||
|
ከተማ |
ቀበሌ |
የቤት ቁጥር |
||||||||
|
1 |
አቶ ታረቀኝ አረጋ |
ኦቶ ታረቀኝ አረጋ |
ጋምቤላ ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
504 ካ.ሜ |
241449/2002 |
ጋምቤላ |
04 |
አዲስ |
633,075.00 |
|
2 |
አቶ ታምራት ነጆ |
አቶ ታምራት ነጆ |
ጋምባሲ ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
275 ካ.ሜ |
1477/ከ3-96/07 |
ባምባሲ |
01 |
አዲስ |
646,099.00 |
|
3 |
አቶ ሚሊዮን ዓባይ ኃይሌ እና ወ/ሮ ያየሽ ስማቸው |
አቶ ሚሊዮን ዓባይ ኃይሌ |
መናኽሪያ ጅማ ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
500 ካ.ሜ |
BMG/125/2007 |
ጁማ ዞን ጊንቢ |
01 |
አዲስ |
650,981.00 |
|
ወ/ሮ ያየሽ ስማቸው |
መናኽሪያ ጅማ ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
424 ካ.ሜ |
0050/13 |
ጁማ ዞን ጌንቤ |
01 |
አዲስ |
659,917.00 |
||
|
4 |
አቶ ፍሬው ካሳ |
አቶ ፍሬው ካሳ |
አዴት ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
190 ካ.ሜ |
ከአገ/112504/12 |
አዴት |
01 |
አዲስ |
1,474,417.00 |
|
5 |
አቶ ጌታቸው መስፍን በላይነህ |
አቶ ጌታቸው መስፍን በላይነህ |
ስታዲዬም ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
400 ካ.ሜ |
SUL/2494/03 |
ሱሉልታ |
|
አዲስ |
9,179,670.00 |
|
6 |
አቶ ኤርሚያስ ጌታቸው አለማየሁ |
ወ/ሮ ራሄል አበራ ገላው እና አቶ መላኩ ተስፋዬ ተሻለ |
በሻሌ ቅርንጫፍ |
ለሆቴልና መዝናኛ የሚሆን ቦታ እና መጋዘን |
3450 ካ.ሜ |
SUL/3801/13 |
ሱሉልታ |
|
አዲስ |
23,277,509.00 |
|
7 |
አቶ ቶኒ ኤልያስ ባዳ |
አቶ ቶኒ ኤልያስ ባዳ |
ባሮ ማዶ ቅርንጫፍ |
መኖሪያ ቤት |
656 ካ.ሜ |
28649/05 |
ጋምቤላ |
05 |
አዲስ |
5,440,260.00 |
በመሆኑም ፡-
- ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተገለጹት አድራሻዎች በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሠራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቲኦቲን የሚያካትት ወይም የማያካትት ለመሆኑ በግልጽ ማስፈር አለባቸው።
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። አሸናፊ የሆነው ተጫራች ደግሞ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ከዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ታህሳስ 8 ቀን 2017 ከቀኑ 9፡30 ሰአት በዋናው መሥሪያ ቤት የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ባንኩ ንብረቶቹን በገዢው ስም ለማዘዋወር ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል።
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 10 24 ወይም 0114 16 97 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ሕብረት ባንክ አ.ማ
