Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Teachers Association Communication (ኦሮሚያ ክልል መምህራን ማኅበር)
  • Address ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ቀበሌ 10 ልዩ ስሙ ማሞ ማዞሪያ ወይም የሸገር ከተማ አስተዳደር ጊቢ አጠገብ ካለው ጊቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114404171
  • Website
  • Deadline02 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኦሮሚያ ክልል መምህራን ማህበር በፌዴራላዊ አወቃቀር መሠረት በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሥር በክልል ደረጃ የተደራጀና ለትርፍ ያልተቋቋመ የሙያ ማህበር ሲሆን በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጄንሲ ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ቁጥር 0344 ዳግም በተቋቋመው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጥላ ሥር የተደራጀ የክልል ማህበር ሆኖ በህገ ደንቡ መሠረት ገቢና ወጪዎቹ ማለትም ከ2005 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ ያሉትን የሂሳብ ሠነዶች በዘርፉ ሥራ የተሰማሩ ድርጅቶችን /Charter Oditor/ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Oromia Teachers Association Communication (ኦሮሚያ ክልል መምህራን ማኅበር)


የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ክልል መምህራን ማህበር በፌዴራላዊ አወቃቀር መሠረት በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሥር በክልል ደረጃ የተደራጀና ለትርፍ ያልተቋቋመ የሙያ ማህበር ሲሆን በበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጄንሲ ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ቁጥር 0344 ዳግም በተቋቋመው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጥላ ሥር የተደራጀ የክልል ማህበር ሆኖ በህገ ደንቡ መሠረት ገቢና ወጪዎቹ ማለትም ከ2005 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ ያሉትን የሂሳብ ሠነዶች በዘርፉ ሥራ የተሰማሩ ድርጅቶችን /Charter Oditor/ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የማህበሩ ዓመታዊ የገቢና የወጪ ሠነዶች በሂሳብ ባለሙያዎች በቅድመ ኦዲት ሥራ ተፈትሾ የተሰናዳ (የተዘጋጀ) በመሆኑ ይሄው ከግምት ገብቶ የሙያ ክፍያ እንዲቆረጥ ስናሳስብ በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የክልሉን የሥራ ቋንቋ /አፋን ኦሮሞ/ መናገር፤ ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፤
  2. በኦሮሚያ ክልል በዚህ ሙያ ተሠማርተው ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
  3. የዘመኑን የመንግሥት የስራ ግብር የከፈሉ፤
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፤
  5. ከዚህ በፊት በክልሉ የተለያዩ የታወቁ ተቋማት ሂሳብ መርምረው ላሳዩት የሥራ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ለዚህ ሥራ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የየዓመቱን የሚሠሩበትን ዋጋ እና ሥራውን የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ አንድ አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ወደ ማህበሩ ቢሮ በመምጣት የምትሠሩበትን ነጠላና ጥቅል ዋጋ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አድራሻ ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ቀበሌ 10 ልዩ ስሙ ማሞ ማዞሪያ ወይም የሸገር ከተማ አስተዳደር ጊቢ አጠገብ ካለው ጊቢ ሲሆን

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

ስልክ ቁጥር ፡- 0114404171/0910168095 ወይም

0912253578/011404170 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

 

ኦሮሚያ ክልል መምህራን ማኅበር

Save Tender