Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Dec 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የሚገኘውን ከሜክሲኮ ወደ ሳርቤት በሚወስደው ዋናው መንገድ ዳር ላይ በሚገኝ ዋና መ/ቤት ያለበት ህንፃ ስር የሚገኘው 120.5 ካሬ ስፋት ያለው ቤት በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  መለያ  ቁጥር: ኢኢግ/ብግጨ/01/2017

የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የሚገኘውን ከሜክሲኮ ወደ ሳርቤት በሚወስደው ዋናው መንገድ ዳር ላይ በሚገኝ ዋና መ/ቤት ያለበት ህንፃ ስር የሚገኘው 120.5 ካሬ ስፋት ያለው ቤት በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተመለከቱትን  ነጥቦች  በማሟላት  ቀርበው  መወዳደር  ይችላሉ።

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታዎችን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፣ በበጀት ዓመቱ ዘርፉ ላይ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ቅጂ፣ የንግድ ስም ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርትፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ለጨረታ የሚያስፈልጉ ቅፆችን አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ብሎክ ፋይናንስ መምሪያ የመጀመሪያው ወለል ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000028606177 በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም ገቢ በማድረግ ፋይናንስ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከራየውን ቤት ከሰነዱ ላይ በተጠቀሱት የስራ ቀናቶች ቦታው ድረስ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤
  4. ተጫራቾች በሚሰጠው ዋጋ መነሻነት 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢኢግ ዋና መስሪያ ሜክሲኮ በሚገኘው ብሎክ A 1ኛ ፎቅ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የእረፍት ወይም በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው የሚከፈትበትን ጊዜ ሳይገኙ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጨረታው ከመዘጋቱ 5 ቀን በፊት በጽሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 0976000836 ደውሎ አከራይ መስሪያ ቤትን መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
  7. ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ በህግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒ እና ኦሪጅናል በተለያየ በሰም በታሸገ ፖስታ በዋናው መ/ቤት በሚገኘው ብሎክ A 1ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ

Save Tender