Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
  • Address ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 557 2734
  • Website
  • Deadline11 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በቃሊቲ-1 እና ቃሊቲ-2 የሚገኙ ለኪራይ የተዘጋጁ ቤቶችን ለማከራየት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን


የጨረታ ማስታወቂያ

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በቃሊቲ-1 እና ቃሊቲ-2 የሚገኙ ለኪራይ የተዘጋጁ ቤቶችን ለማከራየት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወደም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሣተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ድርጅት ከሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ግለሰብ ከሆነ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ፣ ሙሉ ስምና ስልክ ቁጥር በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን በሚገኘው በፋውንዴሽኑ ዋና መ/ቤት በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋውንዴሽኑ የመሰብሰቢያ አደራሽ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና እንደየቤቱ ካሬ ሜትር በካሬ ኪራይ በማባዛት 2% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በባንከ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
    1. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን

ስልክ ቁጥር- 0115572738 አዲስ አበባ

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን

Save Tender