የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብዛት 500,000 የቦሎ መለጠፊያ እስቲከር ህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ.ኢስጽ/ግንአዳ/002/2017
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብዛት 500,000 የቦሎ መለጠፊያ እስቲከር ህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
-
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ከቀኑ 8:30 ይከፈታል፣
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
