የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ቢሮ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ልማት ጣቢያዎች የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያል ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ቢሮ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ልማት ጣቢያዎች የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያል ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. የስፖርት ትጥቅና የስልጠና ማቴሪያል
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ክብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 / አስር ሺህ ብር ብቻ/ በጨረታ ማስከበሪያ በባክ በተረጋገጠ ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአንድ ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስክ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን ፈርማቸውን አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፡፡
- የስፖርት ትጥቅና የስልጠና ማቴሪያል ግዢ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚቆይ ይሆና፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት /መጠን/ እንደአስገላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር / መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፍኬሽን ዝርዝር መሰረት ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
