የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የህትመት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዩብ/ግ/ጨ/10/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የህትመት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማለትም፡
-
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- አሸናፈው ድርጅት ለሁለት ዓመት ውል በመያዝ አገልግሎት መስጠት የሚችል
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት ከላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን የሚገልጽ የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር / ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዩኒቨርስቲው ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000017980517 በመክፈል ደረሰኝ በማቅርብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ፋይናሽያል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ሰነዶችን ኮፒ እዚህ ዶክመንት በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ከ8ኛ ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ 8 የስራ ቀናት ውስጥ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፤
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሀንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ።ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
