Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033 112 50 72
  • Website
  • Deadline29 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

በአ/ብ/ክ/መንግስት በደ/ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ/መቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአ/ብ/ክ/መንግስት በደ/ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ/መቤቱ አገልግሎት የሚውል ፡-

  1. ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና ተያያዥነት ያላቸው እቃዎች
  2. የተለያዩ ቋሚና አላቂ መሳሪያዎች
  3. ልዩ ልዩ ህትመቶች
  4. ልዩ ልዩ የጽዳት እቃዎች
  5. የደንብ ልብስ ጨርቅ እና ጫማ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡

በዚህም መሰረት ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው፣
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ይህ ማታስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን የጨረታ ሠነዶች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቶች ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋውም /ቫቱን/ ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ፖስታ ከነኮፒው በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 6/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 20/2017 ዓ/ም ድረስ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ18ኛው ቀን ማለትም ህዳር 23/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል፡፡ ይህም የሆነው መከፈት የነበረበት ቀን በ16ኛው ቀን ሆኖ እያለ ነገር ግን መጪው ቅዳሜና እሁድ በመሆኑ ነው።
  10. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በሎት ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 112 50 72 ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender