Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ እና ማ/ቤት በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለግብርና የእንስሳት መድሃኒት ለመሀል አንባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለጨቅላ ህፃናት እና ለCBC ማሽን ለመሀል አምባ ማ/ቤት የመንገድ ዳር መብራት ግዢ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::


ለመጀመሪያ  ጊዜ  የወጣ  ሀገር  አቀፍ  ግልፅ  ጨረታ

ማስታወቂያ  መለያ  ቁጥር GGWW/007/2017

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ እና ማ/ቤት በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለግብርና የእንስሳት መድሃኒት ለመሀል አንባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለጨቅላ ህፃናት እና ለCBC ማሽን ለመሀል አምባ ማ/ቤት የመንገድ ዳር መብራት ግዢ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል :: በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO

     ሎት አንድ ፡ ለግብርና የእንስሳት መድሃኒት ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር

     ሎት አንድ ፡ ለጨቅላ ህፃናት እና ለCBC ማሽን ፡ የጨረታ ማስከበሪያ 50000

     ሎት ሶስት ፡ ለመንገድ ዳር መብራት ፣ የጨረታ ማስከበሪያ 30000 ብር ስለሆነም ተወዳዳሪዎች

  1. የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በዘርፍ የተሰማሩበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መምጣት አለባቸው፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴከኒካልና ፋይናንሻያል ዶከመንት ሲያቀርቡ፡ ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ፤ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
  7. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

  1. በማዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
  2. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን፤
  3. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማዕከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 ኪ.ሜ ነው።
  4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡

    ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 0113360631/0113360146

 

የገደባኖ  ጉታዘር  ወለኔ  ወረዳ  ፋይናንስ  ጽ/ቤት

 

Save Tender