Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዲሳ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0463313425
  • Website
  • Deadline19 Nov 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዲሳ


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር 01/2017

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን:-

1. ለፍ/ቤቱ ለችሎት አዳራሽ የሚውል ጎንዝን ማይክ /Gonsin Mic/፣ 2. 3 X 1 አሉሚኒየም እግዳሚ የእንግዳ ወንበር ፣ 3. የመኪና ጎማ መጠኑ 205 R 16 C ብርጅስቶን እና 7.50 R 16 ጀማል ብርጅስቶን ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች:-

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ቫት ተመዝጋቢና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው ፣
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 በተመሰከረለት CPO /BID Bond/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመከፈል በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ከግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ቀርበው መግዛት ይችላሉ ፣
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/ ደጋፊ የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፣
  6. ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽገው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ቤቱ ግፋን ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል ፣
  7. ፍ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፣ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ጌዴኦ ዞን ከፍ/ ፍ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463313425 ወይም 0912455710 ላይ ይደውሉ፡፡

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ዲሳ

Save Tender