ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ከህንጻው ከፊት በኩል ከዋናው አስፋልት መንገድ መግቢያ ያለውን እና በአዲስ መልክ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ቤት ለንግድ መጠቀሚያነት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ስለፈለገ በድጋሚ የወጣ ጨረታ ነው::
የንግድ ቤት ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ከህንጻው ከፊት በኩል ከዋናው አስፋልት መንገድ መግቢያ ያለውን እና በአዲስ መልክ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ቤት ለንግድ መጠቀሚያነት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ስለፈለገ በድጋሚ የወጣ ጨረታ ነው::
በዚሁም መሰረት
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፍኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ማስታወቂያ ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼከ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዶክመንቶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀኖች ድረስ በድርጅቱ የግዥ ክ ፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አድራሻ ይከፈታል፡፡
- ፖስታውን በሰም ሳያሽግ እና ሲፒኦ ሳያያይዝ ሰነድ የሚያስገባ ተጫራች ጨረታው በተከፈተበት እለት ከውድድር ይሰረዛል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር ፡-01115155005/0115518872 ፋክስ 0115518696
ፓ.ሳ.ቁጥር 2365
የቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
