ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፀውን የጥበቃ ካፖርት በጨረታ ለመግዛት ደፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ሕባ/015/17
ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፀውን የጥበቃ ካፖርት በጨረታ ለመግዛት ደፈልጋል፡፡
|
ዝርዝር መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
የጥበቃ ካፓርት |
በቁጥር |
141 |
34,000.00 |
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንከ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ከፍል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 (ስምንት ተኩል) ሰዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 011-4-67-32-08 ወይም 011-4-70-65-41 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
ሕብረት ባንክ አ.ማ
