Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተመደበለት በጀት የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተመደበለት በጀት የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
  2. የአገልግሎት አቅራቢነት ቲን ነምበር ያላቸው፣
  3. የግዡ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ14/2/2017 እስከ 28/2/2017ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከኮ/ቻ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ሰነዱን ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ::
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ኦርጅናል፣ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የእቃ ዝርዝሩን /Specification/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 29/2/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ጊዜው የበዓላት ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  10. በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡
  11. በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በስልክ ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
  12. ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  13. የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው፡፡
  14. መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0333519107 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና

መሰረተ ልማት መምሪያ

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE