የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ 2017 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች ማከማቻ ቤት ለመከራየት ስለተፈለገ የአገልግሎት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በይዞታ ባለቤትነት ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ግለሰቦች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ 2017 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የመድኃኒትና ህክምና መሣሪያዎች ማከማቻ ቤት ለመከራየት ስለተፈለገ የአገልግሎት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በይዞታ ባለቤትነት ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ግለሰቦች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰብ መወዳደር ይችላሉ።
- ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የ2017 ዓ.ም የመንግሥት ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 /ግዢ ኬዝ ቲም/ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከቀኑ 3፡45 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡45 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ቅዳሜ ወይም አሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፣ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው ።
ስልክ ቁጥር 0482121334 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና
ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
