በአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የባህርዳር የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል በተለያዩ ቦታዎች ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ስራ የሚውል የስካፎበዲርግ ጫማ መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የባህርዳር የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል
ክፍል 1
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የባህርዳር የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል በተለያዩ ቦታዎች ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ስራ የሚውል የስካፎበዲርግ ጫማ መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት
- ድርጅታችን በተለያዩ ቦታዎች ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ስራ የሚውል የስካፎልዲንግ ጫማ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በመጋበዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ
-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- ሁሉም ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ ብቻ ቅርንጫፋቸው ባህርዳር ከተማ ከሚገኙ ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገፅ እና ፖስታ ላይ የተጫራቾች ፊርማ እና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
- ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከአሸናፊው ድርጅት ላይ ከገዛው እቃ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ሰነዶች አንዱን እንኳን ባያሟሉ ከውድድር ውጭ መደረጋቸውን ማወቅ አለባቸው::
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻሉም፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በጥራት ባለሙያ ሲረጋገጥ በራሱ ወጭ ለድርጅቱ ንብረት ክፍል ማስረከብ አለበት፡፡ ናሙና የሚያስፈልጋቸው ቀድመው ናሙና አቅርበው ሲጸድቅላቸው ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንደኛ አሽናፊው ድርጅት እቃውን ባያቀርብ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ሁለተኛ አሸናፊው ድርጅት እቃውን ለማቅረብ ፍቃደኛ ከሆነ በአንደኛው አሸናፊ ዋጋ እንዲያቀርብ ሊጋበዝ ይችላል፡፡
- ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን እቃዎች ውለታ ሲይዝ ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ብቻ ቅርንጫፋቸው በባህርዳር ከተማ በሚገኙ ባንኮች ማስያዝ አለባቸው::
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር
0583201019/0933997862/0911883435 ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የባህርዳር
የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማእከል
ባህርዳር
