በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ ለህሙማን የበሰለ የምግብ አቅርቦት ፣ አጠቃላይ የግቢ የህንፃ ክፍሎች የፅዳት ስራ ፣ የአትክልተኛና የጉልበት፤ የጥበቃና ደህንነት ፣ የላውንደሪ አልባሳት ዕጥበት ስራ ፣ የመድሃኒት ሰፕላይ የላብራቶሪ ቅመም (ሪኤጀንቶች) የራጅ እና የህከምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ ለህሙማን የበሰለ የምግብ አቅርቦት ፣ አጠቃላይ የግቢ የህንፃ ክፍሎች የፅዳት ስራ ፣ የአትክልተኛና የጉልበት፤ የጥበቃና ደህንነት ፣ የላውንደሪ አልባሳት ዕጥበት ስራ ፣ የመድሃኒት ሰፕላይ የላብራቶሪ ቅመም (ሪኤጀንቶች) የራጅ እና የህከምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር / ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታል ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናንስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ላይ ጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስ የስራ ሂደት ከፍል ቢሮ ቁጥር 44 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913005480 /0913034113 /0913023571 በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ 20 / ሃያ / ቀን ይቆያል፡፡
- የመክፈቻው ዕለት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው ::
- ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ ከገቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው ::
- ጨረታው በጥቅል ወይም በነጠላ ሊሆን ይችላል ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
