ድርጅታችን ፋሚሊ ሪኒዋል ዓመታዊ የሂሳብ ምርመራውን ቀጥሎ በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት ማሰራት ይፈልጋል ።
ፋሚሊ ሪኒዋል (Family Renewal)
የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ጨረታ
ድርጅታችን ፋሚሊ ሪኒዋል ጤናማ ቤተሰብን ለመፍጠር በስልጠና፥ የምክር/ምከከር አገልግሎት፣ ሁለንተናዊ የቤተሰብ አቅም ማጎልበቻ ፕሮግራሞችን በመስጠት ጠንካራና በመልካም ስነ-ምግባር የታነፀ ቤተሰብን በመገንባት በአገሪቱ ውስጥ በኢኮኖሚያዊና በማሕበራዊ ኑሮ አቅጣጫ ዕድገት ለማምጣት በሚደረገው ርብርቦሽ የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በምዝገባ ቁጥር 3928 ተመዝግቦ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመስራት ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ አገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
ስለሆነም ዓመታዊ የሂሳብ ምርመራውን ቀጥሎ በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት ማሰራት ይፈልጋል፦
- በIPSAS ሰርተፊኬትድ የሆነ/የሆነች
- ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያለው ያላት
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ/የከፈለች
- በዋና ኦዲተርነት የተመዘገቡበት ማስረጃ ያላቸው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታው የሚያስፈልገውን መረጃ ከድርጅቱ ቢሮ በመቅረብና በመውሰድ ታክስን ጨምሮ የሚያስከፍሉትን የአገልግሎት ዋጋ ረቂቅ እንዲሁም የሂሳብ ሰነድ ከደረሰበት ግዜ ጀምሮ የሂሳብ ምርመራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ግዜ በመግለፅ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ በተጠቀሰው አድራሻ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ጨረታውን ያሸነፈ አካል ብቃት ታይቶ ኮንትራቱ እስከ ሶስት ዓመት ሊራዘም ይችላል፡፡
አድራሻ፡- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሳርቤት ኪንግስ ሆቴል አጠገብ እምወድሽ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401
ለበለጠ መረጃ :- የቢሮ ስልክ- 011-369-0966 ወይም
ሞባይል ፡- 0920731959/0969436043/0911-584722
በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፋሚሊ ሪኒዋል
