በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን የድርጅት ቤት ለቢሮ እና ንግድ አገልግሎት እንዲውል በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት (E.O.T.C. House and Building Administration and Development Enterprise)
የንግድ ቤት የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
1. በኢትዯጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆነውን የድርጅት ቤት ለቢሮ እና ንግድ አገልግሎት እንዲውል በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል ።
2. ለቢሮ እና ለንግድ የሚከራየው ቤት አራት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፡-
- የቤት ቁጥር 2ኛ ፎቅ ካሬው 220.14 ሜትር የሆነ ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከሚገኘው ትንሣኤ ሕንጻ ተብሎ በሚጠራው ሕንጻ ላይ የሚገኝ ነው።
3. ማንኛውም ተጫራች ዋጋን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስቀመጥ አለበት፡፡
4. መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኖ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆኑ አለበት-
5. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውኃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል።
6. ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረበውን ቢሮ በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ፓስታ በድርጅቱ ፅ/ቤት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት
7. ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፤ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፤ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፤ የጤና ዘርፍ ከሆነ ሕጉ ከሚፈቅድለት የጤና ቢሮ የተሰጠ ፈቃድ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል
8. ተጫራቾች ሲወዳደሩ ለሚመረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
9. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል።
10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ
በስ.ቁ. 0911- 78-8698
በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ
