በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ሪጅን ለኮልፌ ቀራንዮ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
Public Servants Social Security Administration (የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ሪጅን ለኮልፌ ቀራንዮ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፤
1. የቤቱ ሁኔታ ቪላ ወይም ፎቅ ቢያንስ 500 ካሬ ሜትር እና ከዚያ በላይ ወለል ስፋት ያለው ክፍል ወይም ክፍሎች ያሉት ሆኖ ከላይ የተጠቀሰው ካሬ ወለል በፎቁ መካከል በተከራይ የተያዘ ክፍል የሌለው መሆን አለበት።
2. ቤቱ ኮልፌ ቀራኒዮ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል።
3. ቤቱ ፎቅ ከሆነ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የውሃና የኤሌክትሪከ መስመሮች የተዘረጉለትና እንደአስፈላጊነቱ የሊፍት አገልግሎት እየሰጠ ያለ መሆን አለበት።
4. ቤቱ ራሱን የቻለ ግቢ ቢኖረውም ባይኖረውም ቢያንስ ሁለት መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው እና በቂ መፀዳጃ ቤት ያለው መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ፕላን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው:
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ 100 ብር በመክፈል
መግዛት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሠነድ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ዋስትና ህንጻ ግራውንድ በተዘጋጀው ሳጥን
ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚከፈተው በ8ኛው ቀን 4:15 ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ይከፈታል። 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
አድራሻ፡- ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት አጠገብ ዋስትና የንግድ ማዕከል ግራውንድ ላይ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-23-13
በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት
