የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሸ ኡምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህኝ ተላልፎ የተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሐሙሱ በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጠ የፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአዋሽ ጉመሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመግዛትና ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዊችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሞላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች
- ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨርታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ መዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዓርብ እስከ ሐሙስ ባሉት ሰባት ቀናት ለግልጽ ጨረታ እስከ 3፡45 እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ከሰዓት በኃላ እስከ 9፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታው ሰነድ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ቢሮ የማይመለስ ብር 100።00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) ብር የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ልሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት(እስኬጅል) መሰረት በአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡
| ተ.ቁ | የጨረት ቦታ | የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልክቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት | ግልጽ እና ሐራጅ ጨረታ | ጫማዎች፣ አልባሳት ኮስሞቲክስ፣የመኪና መለዋወጫ ኤልክትሮኒክስ፣ የሞባይል ቀፎዎችና አክሰሰሪዎች፣ ምግብ ነክ የወዳደቁ ብረታብረቶችና ቆራሌዎች፣ የብር ጌጣጌጦች የኮንስትራክሽን እና የኢሌክትሪክ እቃዎች አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ፣ ልዩ ልዩ እቃዎች እና ሌሎች | የግልጽ ጨረታ ዘወትር ሐሙስ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ከሰዓት እስከ 9፡00 | ለግልጽ ጨረታ ዘወትር ሐሙስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ዘወትር ሐሙስ ከሰዓት 9፡45 ሰዓት ጀምሮ |
5 የጨረታው መክፈቻ ቦታ በአዋሽ ቦታ በአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኮሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል
6። ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾቸ ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቅን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7 አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሽነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርባቸዋል።
8 ካላይ በተ ቁ 7 በተገለጸት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጭራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽን ገቢ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
9። ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላለ።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
