በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር 2016 ዓ.ም በበጀት ዓመቱ አንደኛ ዙር የጽህፈት መሳሪያ የደንብ ልብስ እና የጽዳት እቃዎች እና ኮምፒውተር ፕሪንተር እና ፈርኒቸር እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾፕች የዘመኑን ግብር የከፈለ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከገቢዎች ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡብነትን የምስክር ወረቀትና ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘውም ማስገባት ይኖርባቸዋል።
2.የጨረታ አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናል ለወደፊት የመንግስት ግዥ ላይ እዳይሳተፍ ይደረጋል ያስያዘውም የጭዕረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
3. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎችናሙናውን ለእቃ ግምጃ ቤት ማስረከብ አለባቸው ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይም፣እለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈቻ መግዛት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለደንብ ልብስ ና ለጽህፈት መሳሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለደንበል ልብስ ለጽህፈት መሳሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦአ ለጽዳት እቃ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለዲኮር ለሞንታርቦ ለባነር ለመስተንግዶ ለመኪና ኪራይ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለፒርተር ና ኮሚፒውትውር ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የችጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን እቃዎች ቫትን ጨምሮ የአንድ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ መጠየቂቅያ እረድፍ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረትራ ሰነድ ብቻ በመጠቀም መወዳደሪያ ዋጋዎችን ማስገባት ይኖርባቸዋል በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾችን ጨረታ ውስጥ እዳይሳተፉ ያደርጋል።
11. በእቃ ዝርዝር ሰንጠረዥ ውስጥ ተገልጸው ልዩ መለያ በመ/ቤቱ ፍላጎት መሰረት ለመነሻነት የቀረቡ ሲሆን ተጫራቾች የተሻለ አማራጭ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የሚያቀርቡት ልዩ መለያ ካለ ምርመራ በሚለው ረድፍ ውስጥ ማፃፍ ይኖርባቸዋል።
12. ልዩ መለያ ባልጻፈባቸው ክፍት ቦታዎች ላይ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ አይነት ልዩ መለያ የመግግለጽ ግዴታ አለባቸው።
13. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አዳራሻቸውን ፊርማቸውን በእያንዳዱ ሰነድ በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሰነዶቹን በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።
14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
15. ተጫአራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ፖስታ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ብነወረዳ 08/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 312 ማገባት ይኖርባቸዋል።
16. ጨረታው በወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛ የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11 ቀን በስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በወረዳ 08 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 312 ይከፈታል።
17. በጨረታ አስፈላጊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ሳሸነፉበት እቃ በታዘዙት አርደር መሰረት 20% ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው የታዘዙትንን እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ እራሳቸው ማስገባት የሚችሉ መሆን አለበጥ
18. እቃው በሚጓጓዝበት ወቅት ለሚደርሰው ማንኛውም የትራንስፖርት ወጪ በአቅራቢው ይሆናል።
19. በጨረታ ያለፈው አካል ማሸነፉን እደተገለጸ በመስሪያ ቤቱ ውል ወፈጸም ይኖርበታል።
20. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሱ ዝርዝር እቃዎች ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
21። አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተተፍርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
22. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
23. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
24. ለቋሚ እቃ በአካል/ በስፒስፊኬሽን ማሳየት የሚችል መሆን አለበት።
ለበለጠ መረጃ፦ አድራሻ በስክ ቁጥር 011-8-53-89-75 መደወል ይችላሉ።
