Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Jul 2023, 1:03 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ የእንሣት ሐኪሞች ማኅበር /EVA/ ከአውሮፓ ህብረት /EU/ ባገኘው ድጋፍ ብሔራዊ ክልሎች/አማራ ፣ኦሮሚያ።ሶማሊያ/ የእንሣት ሀብት ፕሮግራሞችን ለማጎልበትና የዘርፉን ምርታማነት ይበልጥ ለማማሻሻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት ላይ ይገኛል።ማኅበሩ የእንሣት ልማት ስራዎችን ለማስፋፋት እዲሁም ጠቃሚ ልምዶችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ አመታዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድ እንቅስቃኤ በማድረግ ላይ ሲሆን ለዚሁ የሚያግዙ ጥራት ያላቸው 600 የቆፋ /leather/ እና 60 ሽራ ቦርሳዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሕጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድረጅቶች በጨረታ ው እዲወዳደሩ ማህበሩ በአክብሮት ይጋብዛል።

1.የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውን አበተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝዎች መደራጀታቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረ  ፈጽሞ የተከለከለ ነው ከላይ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።

5. ፍላጎት ያለው ማንኛውም ተጫራች  ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ወደ ማሕበሩ /EVA /ዋና መ/በኢት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ቀርበው የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ማህበሩ ባቀርበው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ በትየገለጸው ዝርዝር /Sepecfication/ መሠረት ዋጋቸውን ከነ VAT በፊት እና በኋላ በግልጽ ሞልተው ሰነዱንም ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ለድርጅት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPOማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ የጨረታው ውጤት እደታወቀ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ የጨረታውን ውጤት እደታወቀ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

9. አሸናፊው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃዎቹን እስከ ማኅበሩ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ +251 115 525 020 ፣09 10 07 88 99፣09 52 67 77 94 ወይም 09 04 32 76 08 ደውሎ ዝርዝር መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ ከእንግሊዝ ኢምባሲ /British Embassy/ ፊት ለፊት 600 ሜትር ገባ ብሎ ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ ይመናሹ ሕናጣ አጠገብ እንገኛለን።

Save Tender