Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Jun 2023, 5:36 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

ሕብረት ባንክ አ.ማ በባለአክሲዮኖች ተፈርመው ዋጋቸው ያለከፈለባቸውን 2,664,210 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺ ሁለት መቶ አስር/አክሲዮኖችን በታች በተዘረዘረው አኳኋን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።


1. የአንዱ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድመቶ ብር /100.00/ ሲሆን ተጫራቾች በመነሻው ዋጋ ላይ በተጨማሪ የሚከፍሉትን ፕሪሚየም ጨምረው የጨረታ ዋጋ መስጠት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛትና በአንድ መቶ ተባዝቶ የሚገኙትን የብር መጠን 1/4 /አንድ አራተኛ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአክሲዮን ብዛትና ዋጋ ባንኩ ባዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ዋጋ ቅጽ በመሙላት የኢትዮጵያዊ ዜኘት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያ ማስረጃ ኮፒ በማያይዝ ከጨረታ ማስከበሪያው/ሲ.ፒ.ኦ/ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂአይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህብር ታወር ሕንጻ 24ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ቺፍ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ  ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።የጨረታው ማመልከቻ ቅጽ ከባንኩ ድረገጽ /www.https./www.hibrtbank.com.et/Share-Form/ወይም ከባንኩ ፋይናሺያ አካውንቲንግ መምሪያ የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይንም ከባንኩ ቅርጫፎች ማግኘት ይችላል።

4.ጨረታው ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፤30 በሕብር ታወር ሕንጻ 4ና ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ካፍቴሪያ ይከፈታል።

5. ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች ተሽጠው እስከ ሚጠናቀቁ ድረስ ከፍተኛ ዋጋ ያቀእረቡ ተጫራቾች ከፍተኛ ዋጋ ካቀረበው ጀምሮ እደቅደም ተከተላቸው አሸናፊ ይሆናሉ። ተጫራቾችች የተጫረቱበትን ያህል አክሲዮኖች ባያገኙም መጨረሻላይ የሚተርፉትን አክሲዮኖች ባቀረቡት ዋጋ ለመግዛት  ይገደዳሉ።

6. ለሽያጭ የቀረቡት አክሲዮን ቁጥር እስከ ግንቦት 30ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባላክሲዮኖች በሚከፍሉት የአክሲዮን ቁጥር መጠን ሊቀነስ ይችላል።

7. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ኢትዮጵያዊ ዜኘት ያላቸውና ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው የሚይስረዳ ያገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መንጃ ፍቃድ ፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያና ፓስፖርት ከጨረታው ጋር በኤንቨሎፕ ታሽጎ የሚቀርብ ሲሆ ዋናው በጨረታ መክፈቻ ዕለት መቅረብ አለበት። የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ በአክሲዮን ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመ እና የድረጅት መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ በጨረታው መክፈቻ ዕለት ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ ነው።

8. ትውልደ ኢትዮጵያ የሆነ የውጭ ሀገር ዜኘት ያላቸው ተጫራቾች 1/4 ክፍያ ማስያዝ እንዲሁም ጨረታ ካሸነፉ ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ብቻ ሲሆን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕብር ታወር ቅርጫፍ በኩል ይስተናገዳል።

9. አሽናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮበ15/አስራ አምስት/ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ለጨረታ በማውጣት ይሸጣሉ።

10. ሕጋዊ ሰውነት ባላችው ድጅቶች ስም የሚጫረቱ ወይም በውክልና ለሚጫረቱ በጨረታው ለመሳተፍ ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የተመዘገበ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን ተወካይ በጨረታው መክፈቻ ዕለት ማቅረብ አለበት።

11. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችና ሌሎች ሕጎች ተፈፃሚነት አላቸው።

13. ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኢትዮጵያ ዜኘት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሚያሳይ ማስረጃእና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ተያይዞ ካልቀረበ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም።

14. ለተጨማሪ መረጃ የባንኩ ፋይናሺያል አካውት መምሪያ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል በስልክ ቁጥር 0114-704932 ኧዲሁም የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114-700315/47 መጠየቅ ይቻላል።

Save Tender