Tender Detail

Tender Details

  • Deadline14 Apr 2023, 10:37 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

ገርጂ 3 የጋራ ህንፃ ባለቤቶች ኃላ/የተወ/የህ/ሥ/ማህበር ከ2001/2002 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2014/2015 ዓ.ም. ያለውን ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴ የሚመረምርለት የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል


የውጭ ኦዲተር አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ገርጂ 3 የጋራ ህንፃ ባለቤቶች ኃላ/የተወ/የህ/ሥ/ማህበር ከ2001/2002 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2014/2015 ዓ.ም. ያለውን ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴ የሚመረምርለት የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የምታሟሉ የተፈቀደላችሁ የውጭ ኦዲት ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10/አሥር/ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመግዛት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ፕሮፖዛላችሁን በማዘጋጀት በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያለው፤
  3. ከኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ /AABE/ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል!
  4. በህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/09 መሰረት መሥራት የሚችል፤
  5. ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዝብ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችል፤
  6. የተደራጀ ቢሮ የሥራ ግብዓት እና የተሟላ አድራሻ ያለው፤
  7. የተለያዩ ድርጅቶችን ዓመታዊ ሂሳብ የመመርመር ልምድ ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  8. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሚያቀርብበት ጊዜ የሞላው ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በማለት በግልጽ ለይቶ መሙላት ይጠበቅበታል።
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን ከሞሉ በኋላ የማህበሩ ቢሮ በሚያዘጋጀው የጨረታ ፖስታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  10. በጨረታው ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ስለማሸነፉ በተገለፀለት 10/አሥራ/ ቀናት ውስጥ ውል በመዋዋል ሥራ መጀመር የሚችል መሆን አለበት።
  11. ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት በማህበሩ ጽህፈት ቤት ይከፈታል።

የማህበሩ አድራሻ፡- አዲስ አበባ ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፣ ወረዳ 14 ፣ ገርጂ 3 ኮንደሚኒየም ግቢ

(ሳንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት) ቢሮ ቁጥር ኮሚናል 8

ስልክ ቁጥር 011 639 4469

የቦሌ ገርጂ 3 የጋራ ህንፃ ባለቤቶች ኃላ/የተወ/የህ/ሥ/ማህበር

Save Tender