የንብረት የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አን ኢንተርናሽናል 2/የተ/የግ/ማህበር እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ዮሐንስ ኪዳኔ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/127727 በ30/03/2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሚገኝ ንብረት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 10,715 (አስር ሺ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር) መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ be3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
