በአለርት ሆስፒታል ህሙማንንም ሆነ ሰራተኞችን ከኢንፌክሽን ለመከላከል የፅዳት አገልግሎት በአለም ጤና ድርጅት በሚያዘው ስታንዳርድ መሰረት 24/7 ቀናት እንዲሰራለት እንዲሁም የህሙማን ረዳት የአገልግሎት ስራን በውጭ አገልግሎት ሻጭ ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አለ/ግ/ጨ/002/2015 ዓ.ም.
በአለርት ሆስፒታል ህሙማንንም ሆነ ሰራተኞችን ከኢንፌክሽን ለመከላከል የፅዳት አገልግሎት በአለም ጤና ድርጅት በሚያዘው ስታንዳርድ መሰረት 24/7 ቀናት እንዲሰራለት እንዲሁም የህሙማን ረዳት የአገልግሎት ስራን በውጭ አገልግሎት ሻጭ ድርጅት ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
- ሎት 1 የፅዳት አገልግሎት ፣
- ሎት 2 የህሙማን ረዳት አገልግሎት ግዥን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች:-
- ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ በስማቸው ያለ
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች እና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ ቁጥር ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን
- ለሎት 1 - ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- ለሎት 2 - ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ አለርት በሚል ስም በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። በባንክ ጋራንቲ ከሆነ የ120 ቀናት ዋስትና መቅረብ አለበት።
- ስለ ጨረታው የሚገልፀውን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከአስተዳደር ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- እያንዳንዱ ተጫራች በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ፀንቶ ይቆያል። ተጨማሪ ቀን ካስፈለገ ለሁለም ተጫራቾች በደብዳቤ የሚገለፅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሆኖ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም ተደርጎባቸው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4፡30 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከፍ/ቤት የተሰጠውን ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ወይም ከውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸው ፣ ፊርማቸውና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መግለጽ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ ኤንቨሎፖች (ቴክኒካል የመወዳደሪያ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦሪጅናልና አንድ የፋይናንሻል ኮፒ) ማቅረብ አለባቸው። በድምሩ አራት ሰነዶች
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
አለርት ማዕከል የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 347 1601 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አለርት ሆስፒታል
