የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፋርም አፍሪካ ፣ ከዎልዝ ሀንገር ላይፍ ጀርመን ፣ ኢንጀንደር ሄልዝ እና ከሲሲ ፋድ ካቶሊክ ፈረንሳይ ፣ የተረከባቸውን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከቅድስት ፍራንሲስ የሉድ እና ጉድ ኔቨርስ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በመለዋወጫ መልክ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፋርም አፍሪካ ፣ ከዎልዝ ሀንገር ላይፍ ጀርመን ፣ ኢንጀንደር ሄልዝ እና ከሲሲ ፋድ ካቶሊክ ፈረንሳይ ፣ የተረከባቸውን የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከቅድስት ፍራንሲስ የሉድ እና ጉድ ኔቨርስ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በመለዋወጫ መልክ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪዎቹ በሚገኙበት ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ የኒያላ ኢንሹራንስ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ፊት ለፊት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ከሚስትቡሽ ጋራጅ ወይም ደሳለኝ ግሮሰሪ አጠገብ በሚገኘው ባለስልጣኑ በተከራየው መጋዘን እና ቤላ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3:30 - 9:30 መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከባለስልጣን መ/ቤቱ ፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት ክፍል የንብረት ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) እየከፈሉ ቸርቸር ጎዳና ከሚገኘው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መ/ቤት በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን እና እሁድ ጨምሮ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአምስተኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (ሲፒኦ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስም አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። አሸናፊ ለሆኑት ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ሲያስገቡ ያሲያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል ።
- ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4:30 7ኛ ፎቅ በሚገኘው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉትን የተሸከርካሪ ዋጋ በ3 ቀናት ከፍለው በ3 ቀን ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ (ሲ.ፒ.ኦ) ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታ ያሸነፉ ተጫራቾች ያገለገሉ ንብረቶችን በተመለከተ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- ሊብሬ ለጠፋበት (ለሌለው) ተሸከርከሪ ገዢው ሊብሬ የሚያወጣ ይሆናል።
- ማንኛውም ወጪ በገዢው የሚሸፈን ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 011 558 2376 ወይም 011 558 2437
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን
