የሞተር ሳይክል የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ፍሬህይወት ጋሻው እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አሸናፊ አበጀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 127563 ቀን 18/10/2013 ዓ.ም. እና በመ/ቁ 94794 በ3/7/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ የሚገኝ የሠ/ቁ 2-8335 አ.አ የሆነ ሞተር ሳይክል የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር ግምቱ 40,000 (አርባ ሺ ብር) ሆኖ የስም ማዞሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾችተመዝግበው እንደተጠናቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው የፌዴራል የፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
