Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Jul 2022, 4:11 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Disposal Sale

የንብረት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አን ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ዮሐንስ ኪዳኔ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/127727 በ30/03/2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የሚገኝ ንብረት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 10,715 (አስር ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር) መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 18 ቀን 2014
ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም
ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጎድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

READ MORE