የጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2019
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያለት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ጥራቱን በጠበቀ ስካን በማድረግ ኦንላይን የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO ለእያንዳንዱ ኮድ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ አክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን የግልጽ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ህዳር 18 ቀን 2019 ጀምሮ ህዳር 25 ቀን 2019 ጠዋት 4:00 ሰዓት በ8ኛው ቀን ላይ ይዘጋል።
- ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም
- ማንኛዉም ተጫራች የሰጠዉ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ዉጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ዉድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል
- ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልከተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
- አሸናፊዉ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በዉስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ተጫራጮች የሚጫኑት/የሚያቀርቡት ሠነድ ጥራቱን በጠበቀ መሳሪያ ስካን የተደረገ እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ብቻ እንዲያቀርብ ይመረጣል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ማሳሰቢያ: ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን!
የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-5511 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:
ለበለጠ መረጃ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር:- 046-212-53-96 / 046-220-1936 ይደውሉ
የቴሌግራም ገፃችን:-https://t.me/hawassaaweqaqed (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018)
