Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ አካባቢ በሚገኛው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ህንፃ 15ኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼይን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-38-98
  • Websitehttp://www.ethiopianelectricutility.gov.et/
  • Deadline16 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 1000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateታህሳስ 07 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30
  • Sector Sales , Disposal Sale , Vehicle and Spare Parts , Vehicle Sale

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-08/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ሎት የሚወገደው ንብረት ዓይነት የሚገኙበት ቦታ መለኪያ ብዛት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የጨረታ መዝጊያ የጨረታ መክፈቻ
1 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ኮተቤ ጋራዥ በቁጥር 16 የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% ታህሳስ 07 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ታህሳስ 07 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር(EEU Minor Account No, 1000068699332) የማይመለስ ብር 1000.00(አንድ ሺህ) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ የናይል ኢንሹራንስ ዋናው መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜክሲኮ የናይል ኢንሹራንስ ዋናው መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል::
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት::
  7. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Summary
Ethiopian Electric Utility invites bids to buy 16 used vehicles, sold as-is at its Kotebe garage.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender