የደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት፣ የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስና የመኪና እቃዎች ግዥ
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማችን ውስጥ ያሉ ሴክተር መ/ቤቶች በጠየቁት የግዥ ፍላጎት ለመፈጸም ከዚህ በታች ባሉት ሎቶች መሰረት:-
ሎት 1 ደንብ ልብስ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 3 የጽዳት እቃ
ሎት 4 ቋሚ እና አላቂ ዕቃ ሎት 5 - ኤሌክትሮኒክስ ሎት 6-የመኪና እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ይጋብዛል::
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ መረጃ ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- የግዥ መጠኑ ከ500,000 ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ
- የሚገዛውን የእቃ ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል ወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-24 በመሄድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና በየሎቶቹ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ 2% በማስያዝ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች በየሎቶቹ የጨረታ ሰነዱን ኦሪጂናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በማሸግ ወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት በማስገባት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል::
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ከመከፈቻው 5 ቀን በፊት በአካል ወይም በስ.ቁ 0912354575/0919972162 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
ማሳሰቢያ
- መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት እቃዎቹ መቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው ለ45 ቀናት ጸንቶ ይቆያል::
የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት
Summary
Woreilu Town Administration Finance Office (South Wollo, Amhara) invites bids in six lots: uniforms, stationery, cleaning items, fixed and consumable items, electronics, and vehicle parts.
