በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ /መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በመ/ቤቱ ላሉ አጠቃላይ ሰራተኞች ደረጃውን የጠበቀ የሰራተኞች ሙሉ ደንብ ልብስ ከነ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ /መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ /መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በመ/ቤቱ ላሉ አጠቃላይ ሰራተኞች ደረጃውን የጠበቀ የሰራተኞች ሙሉ ደንብ ልብስ ከነ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1ኛ. ለ2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችል
2ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችል
3ኛ. የአገልግሎት ክፍያ 2% ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ
4ኛ. በስራ ዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለውና ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችል
5ኛ. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችል
6ኛ. አሸናፊው ተጫራች /ድርጅት/ ያሸነፈውን ደንብ ልብስ እስከ ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አቅርቦ ማስረከብ የሚችል
7ኛ.አሸናፊው ከቦታው እስከ ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሲያቀርብ የማስጫኛና ማውረጃ ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ መሸፈን የሚችል
7ኛ. የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ጥራቱን የጠበቀ ማቅረብ ግዴታ አለበት
8ኛ. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን የደንብ ልብስ ከማቅረቡ በፊት ከእያንዳንዱ ናሙና በማቅረብ ከመ/ቤቱ ጋር መስማማት/መተማመን/ አለበት::
9ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ cpo በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከታወቀ የግል ባንኮች የተረጋገጠ ቼክ፣ ለወንዶች ደንብ ልብስና ለጥበቃ 15,000 ለሴቶች ደንብ ልብስና ለካፌ ሰራተኞች 15,000 በቅደምተከተላቸው መሰረት ማስያዝ የሚችል
10ኛ. የጨረታ ሠነድ ካፋ ዞን ቦንጋ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ፋይናንስ ቸል ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 700 ብር/ሰባት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን
11ኛ. የዋጋ ማቅረቢያ የእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚችል
13ኛ, ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል
14ኛ. የጨረታ ሣጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት በ16ኛ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፤30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ማሳሰቢያ-የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ላይ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን አያስተጓጉልም::
በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ጨረታውን ያሰርዛል::
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0913057215 /0917824561
