የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአሰላ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባና ባህርዳር መጋዘኖች የሚገኙ 102,414.96 ኩንታል ባቄላ፣ ነጭ፣ ሠርገኛ፣ ማኛ እና ቀይ ጤፍ ለመሸጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 03/2019)።
Ethiopian Trading Businesses Corporation (የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የተለያዩ እህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የገዛቸውን የተለያዩ የጥራጥሬ እና የብርዕ እህሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። የእህል አይነቶች፡-
| ቅ/ግብይት ማዕከል | ምርቱ የሚገኝበት መጋዘን /ጣቢያ | የምርት አይነት | መጠን በኩ/ል | የጥራት ደረጃ | መግለጫ |
|---|---|---|---|---|---|
| አሰላ | በቆጂ | ባቄላ | 470.54 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አሰላ | ሎሌ | ባቄላ | 220.14 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | ኢታያ | ባቄላ | 5,462.54 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | አ/ርቢ | ባቄላ | 5,775.69 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 197 | ማኛ ጤፍ | 2,100.00 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 195 | ነጭ ጤፍ | 6,364.66 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 128 | ነጭ ጤፍ | 11,202.58 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 162 | ነጭ ጤፍ | 351.59 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 127 | ሠርገኛ ጤፍ | 994.23 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 128 | ሠርገኛ ጤፍ | 15,030.79 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አ/አ ግብይት ማዕከል | 195 | ሠርገኛ ጤፍ | 17,428.26 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | አዳማ | ሠርገኛ ጤፍ | 3,597.79 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | አርሲ ሮቤ | ሠርገኛ ጤፍ | 134.83 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | ኢታያ | ሠርገኛ ጤፍ | 17,289.50 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| ባህርዳር | ባህርዳር | ሠርገኛ ጤፍ | 1,854.50 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዲስ አበባ ማዕከል | 128 | ቀይ ጤፍ | 404.20 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዲስ አበባ ማዕከል | 195 | ቀይ ጤፍ | 1,130.60 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | አዳማ | ቀይ ጤፍ | 861.52 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| አዳማ | ኢታያ | ቀይ ጤፍ | 11,741.00 | 1ኛ ደረጃ | ለሰው ምግብ አገልግሎት |
| ድምር | 102,414.96 | ||||
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን የመመዘኛ መስፈርቶች በሚያሟላት በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፤
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው በእህል ጅምላና ችርቻሮ ንግድ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ምርቱን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ምርቱ በሚገኝበት መጋዘን በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 6:30 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በዘርፉ ስም (የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ ወይም Grain and Coffee Trading Business Unit) በሚል ብቻ የተሰራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
- በከፊል መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከተዘረዘሩት ምርቶች ውስጥ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጠው መጫረት ይችላሉ፤
- ለጨረታ የቀረበው ምርት መጠን በ10% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፤
- በግልፅ የማይነበብ ትክክለኛውን የዋጋ አቀራረብ ሥነስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሠነድ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቾችን አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል፤
- ተጫራቾች የሚገዙበትንዋጋ እና የቴክኒክ ሰነዶች በመለየት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ሰነዳቸውን በሁለት ኢንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥር 03/2019 በማለት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በኮርፖሬሽኑ ህንፃ ቁጥር 2 አራተኛ ፎቅ የሽያጭ ቢሮ ቁጥር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይሆናል፤
- በአዲስ ዘመን እና በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፤
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በዘርፉ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ይሆናል፤
- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ በዘርፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ ውል ፈርሞ መክፈልና በጨረታው ያሸነፈውን እህል መረከብ ይኖርበታል፤ አሸናፊው በ10 ቀናት ውስጥ ውል ፈርሞ ገንዘብ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፤
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ምርቱን ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዝ ወጪ ይሸፍናል፤
- ዘርፉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 16 78 80 ወይም 09 39 57 57 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Summary
Ethiopian Trading Businesses Corporation sells 102,415 quintals of first-grade grain (faba beans and white, mixed, magna and red teff) held in Asella, Adama, Addis Ababa and Bahir Dar warehouses. Licensed grain traders may bid for one or more items.
