Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline25 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ግምቱ 1/4ኛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateታህሳስ 16 ቀን 2019 ዓ.ም ምዝገባ እንደተጠናቀቀ፣ የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Sector Foreclosure , House and Building , House and Building Maintenance , Sales

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘውን 694.88 ካ/ሜ ቦታ ያለውን ቤት (የቤት ቁጥር 001) በመነሻ ዋጋ ብር 44,420,669.95 ለመሸጥ ያወጣው የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አለም መካ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ወልዴ በረካ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/102803 በ2/10/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ11/11/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/107090 በ14/5/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በቀድሞ 25 በአዲሱ 13 ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ወ13/ ውዝ01/66/2199/00 የቤት ቁጥር 001 የሆነ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የቦታ ስፋት 1,247.46ካ/ሜ ሲሆን በአስኮ ሚኪሊ ላንድ ፡ መንገድ ፕሮጀክት ምክንያት በከፊል የፈረሰ እና ካሳ የወሰዱ እና ከ1,247.46 ካ/ሜ ላይ 448.76 ካ/ሜ የተቀነሰባቸው ቢሆንም በ39/40ኛ ዙር መንገድ ጥናት እና በአስኮ ሚኪሊለንድ መንገድ ፕሮጀክት ዲዛይን ማሻሻሉ ምክንያት ካሳ ያልተከፈላቸው እና 2ኛ ዙር የሚቀነስባቸው የቦታ ስፋት 103.82ካ/ሜ የሚቀነስባቸው ሲሆን ቀሪው የቦታ ስፋት694.88ካ/ሜ ቤት ድርጅት ስለሆነ ካፒታል ጌን ታክስ የሚከፍለው የፍ/ባለዕዳ ሲሆን ገዥው አካል ቤቱን የሚረከበው የክ/ከተማው መሬት አስተዳደር በላከው እስኬች መሰረት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 44,420,669.95 ( አርባ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ከ95/100 ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
Federal Courts Judgment Execution Office auctions a house (No. 001) in Addis Ketema Woreda 13, Addis Ababa, on a remaining 694.88 sq.m plot after road-project deductions. The buyer pays the transaction tax; viewing is arranged before the auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender