የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባህርዳር ቅርንጫፍ ለካፍቴሪያ፣ ለሬስቶራንትና ለህፃናት ማጫወቻ የሚውሉ ቦታዎች ኪራይ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት
ለተለያዩ አገልግሎት የሚከራዩ ንብረቶች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር OR 02/2019
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በድርጅቱ ባህርዳር ቅርንጫፍ በተለምዶ ማንን ወይም ጊዮርጊስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሀይቁ በቅርብ ርቀት ላይ ዘመናዊ G+2 ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ህንፃ በማስገንባት አገልግሎት ላይ ያዋለ ሲሆን ቅርንጫፉ ከሚገለገልበት ውጪ ያሉ ለካፍቴሪያ፤ ለሬስቶራንት እና ለህፃናት ማጫወቻ የሚውሉ ቦታዎችን ባሉበት አሁናዊ ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 (ሶስት) አመት በሚቆይ እና ከ3 አመት በኋላ አከራይና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት የኪራይ ዘመኑ ሊራዘም ወይም ሊቋረጥ በሚችልበት አግባብ ለማከራየት ይፈልጋል::
በመሆኑም ለመከራየት እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ፍላጎቱና አቅሙ ያለው ማንኛውም ሰው/ድርጅት በኢትዮጵያ ህግ የተቋቋመና የሥራ ፍቃድ ያለው ወይም ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለሆነ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከጨረታው የመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረበ ተወዳዳሪ በኪራይ ለማስተላለፍ ይፈልጋል::
በመሆኑም ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ያለው አካል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ህዳር 16 ቀን 2019ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በምከፈል ዝርዝር ጉዳይ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከባህርዳር ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል።
ለኪራይ ጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ኮፒ በመያዝ ዘወትር በድርጅቱ የሥራ ሰዓት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 2:00 እስከ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከቀኑ 2:00 እስከ 6:00 ሰዓት በባህርዳር ከተማ የድርጅቱ ቅርንጫፍ በሚገ[...] በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ::
የጨረታውን ሰነድ የገዛ ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን ያሰፈረበትን የጨረታ ሰነድ ከህዳር 16ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 28 ቀን 2019ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እና የጨረታ ሳጥኑ እስከ ሚታሸግበት ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 8:00 ሰዓት በባህርዳር ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሠዓት 8:00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም::
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ነገር ሲገጥመው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918765584 ወይም 0953680904 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል::
