Tender Detail

Tender Details

  • Company City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 62 14 57
  • Websitehttps://addisconstructionwork.gov.et/
  • Deadline03 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት1 ብር 200,000.00፤ ሎት2 ብር 150,000.00፤ ሎት3 ብር 75,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30፣ በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ
  • Sector Electrical And Electromechanical , Networking Equipment And Installation , Construction Materials And Raw Materials

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የዳታ፣ የካሜራና የኔትዎርኪንግ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ

City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የተለያዩ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ እና የዳታ፣የካሜራ፣የኔትዎርኪንግ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/11/2019

ድርጅታችን ለአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ G+4 ሕንጻ ግንባታ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ እና የዳታ፣ የካሜራ፣ የኔትዎርኪንግ እቃዎች አቅርቦትና ገጠማ የሚያስፈልጋቸው ግብዓቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም ከዚህ በታች በተገለጹት ሎቶች መሠረት ማለትም፤

  • ሎት 1 TELE DATA SYSTEM, CCTV SYSTEM (SUPPLY & FIX ) ከነገጠማው, FIRE ALARM SYSTEM (SUPPLY & FIX ) ከነገጠማው, NETWORK SWICH SYSTEM (SUPPLY & FIX ) ከነገጠማው
  • ሎት 2 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ግብዓቶች
  • ሎት 3 የተለያዩ የሳኒተሪ ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ግልጽ ጨረታ ማውጣት ይፈልጋል።
  1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ ምዝገባ ሠርተፍኬት የጨረታ መሳተፊያ ክሊራንስ ከገቢዎች መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C. C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
    • ለሎት 1 ለእያንዳንዳቸው ከላይ በዝርዝር ለቀረቡት 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
    • ለሎት 2 ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
    • ለሎት 3 ብር 75,000.00 / ሰባ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantees) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ሐሙስ ሕዳር 24/2019 ከሰዓት 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.C.R.D.A አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0911060918/0920276648

የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት

Summary
Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise invites bids to supply and install tele-data, CCTV, fire alarm and network systems, electrical and sanitary materials for a water and sewerage building.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የአሸዋ፣ ሀርድ ኮር፣ ሰሌክት ማቴሪያልና ፑሚስ ግዥ ከነትራንስፖርቱ

READ MORE
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የህጻናት መጫወቻ ሜዳ መሳሪያዎችና የግንባታ ዕቃዎች ግዥ

READ MORE
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የህንፃ መሳሪያዎች ግዥ

READ MORE