በጉለሌ ክ/ከተማ የአዲስ ብርሃን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2019)።
አዲስ ብርሃን ቅ/አ/አ/መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- በዘርፉ የተሰማሩበት ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ(Tin) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ለተጠቀሱት እቃዎች የማይመለስ በሎት ብር100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች ዋጋ የተሞላበት ማቅረብ ግዴታ ነው ካልሆነ ግን ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች በአጠቃላይ ብር 10,000 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን በአሥረኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11:00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራአንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ/ግ/ን/አስ/ገ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት የታዘዙትን የተለያዩ የግንባታ ስራዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ 10%ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሎቶች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ 20% የመጨመር የመቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው። በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያ የማያሲዙ ተጫራቾች አሰት የሚጨምሩ (አምራች ሲሆኑ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል በሚያመጡት ደብዳቤ ይስተናገዳሉ። አድራሻ፡- በጉለሌ ክ/ከተማ ቀጨኔ በድሮ ወረዳ 5 ባሁኑ ወረዳ 4 ከፍ ብሎ ቀበሌ 07/17 መዝናኛ ክበብ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡-0111568312 ይደውሉ
አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Summary
Addis Birhan Kindergarten, Primary and Middle School (Kechene, Gulele sub-city, Addis Ababa) tenders various construction works funded from its internal revenue. Licensed, VAT-registered suppliers registered with the Finance Bureau may bid.
